Posted in Uncategorized

የተለያዩ የስዊች አይነቶች ክፍል 9

ስዊች ማለት ማብሪያ ማጥፊያ ማለት ነዉ ። የማንኛዉም ስልክ ማብሪያ እና ማጥፊያ ከሚከተሉት ሁለት መንገዶች በአንዱ ይገኛል ።

  1. አናቱ ላይ ወይም ጎኑ ላይ በስዊች የሚበራ እና የሚጠፋ ፤ ምሳሌ ፦ 3310፣6070 ፣ 6300 ፣ 6131
  2. የስልኩ ቀይ ክፍል /በተን/ እንደ ማብሪያ እና ማጥፊያ የሚያገለግል ፤ ምሳሌ ፦ 1110 ፣ 1100 ፣1600 ፣ V3 ፣ X660 ፣ x640 ፣ C100
  3. ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተዉ የመጀመሪያው አይነት ስዊችን ይሆናል ።

ስዊቾችን ለመንቀልም ሆነ ለመትከል ካዉያ እንጠቀማለን ። ስዊቾች በኮንቲኒቲ መስራትና አለመስራታቸዉን ማረጋገጥ እንችላለን ። አብዛኛውን ጊዜ ከስዊች አጠገብ ስዊቺንግ ሬዚስተር ይኖራል ። እነዚህ ሬዚስተሮች በአንድ ጎን ከስዊች አንድ እግር ጋር እና በአንድ ጎን ደግሞ ከፓወር አይሲ ጋር ወይም ከግራዉንድ ኮንቲኒቲ ያሳያል ። ስዊቺንግ ሬዚስተሮችን በሌላ ስዊቺንግ ሬዚስተር መተካት ይቻላል ። አንድ ስልክ የሥዊች ችግር ቢኖርበትም ቻርጅ ሲያደርግ ያሳየናል ። የስዊችን ፓዘቲቭ እና ንጋቲቭ እግሮቹን በትዊዘር ማገናኘት ወይም በብረት በማነካካት ስልኩን ማብራት ይቻላል ። ፓዘቲቭ እና ኔጋቲቭ እግሮቹን በሊድ ብናገናኝ ደግም ስልኩ ባትሪ ሲገባበተት ቀጥታ ይበራል ።የዚህ ስልክ ችግር ስልኩን ማጥፋት የሚቻለዉ ባትሪዉ ከስልኩ ሲወጣ ብቻ ነዉ ። እንደዚህ አይነት አማራጭ የምንጠቀመዉ የስዊች ማስቀመጫ ኢንተርፌሶች ከቦርዱ ተቦጭቀወዉ የጠፋ ሲሆን ብቻ ነዉ ።

ሁሌም አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርሶ like , share, comment ያድርጉ

#ኑሩ_ዲሽ

ለበለጠ መረጃ ©0945686310