Posted in Uncategorized

የኖኪያ ስልክ ትዉልዶች ክፍል 3

  1. ዲሲቲ ስሪ (DCT3) :- እነኚህ ስልኮች የድሮ ስልኮች ሲሆኑ በሙሉ ባለጥቁር ስክሪን ናቸዉ ። ምስሉ ላይ እንደሚታየዉ እነዚህ ስልኮች ኦዲዮ አይሲ : ፓወር አይሲ : ዩአይ አይሲ እና ቻርጅ አይሲ የሚገኙት ራሳቸዉን ችለዉ እና ተነጣጥለዉ ነዉ ። እነዚህ ስልኮች ላዉድ ስፒከር የላቸዉም ። ምሳሌ :-3310: 2100 : 3410 ለዉድ ስፒከር የሌለዉ ስልክ በሙሉ ግን ዲሲቲ ስሪ አይደለም ። ለምሳሌ 1100 ስልክ ዲሲቲ ስሪ ያልሆነ ነገር ግን ላዉድ ስፒከር የሌለዉ ስልክ ነዉ ።
  2. ዲሲቲ ፎር (DCT4) :- እነዚህ ስልኮች ከዲሲቲ ስሪ የሚለዩት ተሻሽለዉ የተሰሩ በመሆናቸዉ ነዉ። ሬዲዮ : የድምጽ መቅረጫ : ካሜራ እና ኢንፋራሬድ ሊኖራቸዉ ይችላል ። እነዚህ ስልኮች ኦዲዮ አይሲ : ፓወር አይሲ: ዩአይ አይሲ እና ቻርጅ አይሲ አንድ ላይ እናገኛቸዋለን ። አራቱን አይሲዎች አንድ ላይ የሚይዘዉ አይሲ ዩኢኤም (UEM) ይባላል ። ዲሲቲ ፎር ስልኮች በአብዛኛው ባለቀለም ስክሪን ይጠቅማሉ ። ምሳሌ :-1600 : 1110: 6030: 2630 :2310 ባለቀለም ያልሆኑ ዲሲቲ ፎር ስልኮች ምሳሌ 1100 እና 1110
  3. ደብሊዉ ዲቱ (WD2):- እነዚህ ስልኮች ደግሞ ሜሞሪ ካርድ እና ብሉቱዝ ጨምረው የመጡ እና ሰፋፊ ስክሪን ያላቸዉ ስልኮች ናቸዉ እነዚህ ስልኮች ጠፍተዉ ስናበራቸዉ የመዘግየት ባህሪ አላቸዉ ። ልክ እንደ ዲሲቲ ፎር ስልኮች ዩኢኤም አይሲ አላቸዉ ።
  4. ቢቢ ፋይቭ (BB5):- እነዚህ ስልኮች ዘመናዊ ሲሆኑ ከተወሰኑ ስልኮች (N70, N72, 6630, 6680, N90, N91 የመሳሰሉ ጥቂት ስልኮች) በስተቀር ትንሹን ሜሞሪ ካርድ ይወስዳል ። ቪዲዮ ኮል የተጀመረዉ እነዚህ ስልኮች ትዉልድ ነዉ ። ከሀርድዌር አንጣር ስንመለከታቸዉ 2 ሲፒዉ እና 2 ፓወር አይሲ ይኖራቸዋል : ይህ ካልሆነ ደግሞ አንድ ሲፒዩ እና 2 ፓወር አይሲ ይኖራቸዋል ። ምሳሌ :-6300,N70, 3110, X2, C2, C3, 6085, 3110, 5300, 3109

ኖኪያ ትዉልድ |የፒዩ ብዛት |የፓወር አ ብዛት

DCT3 | 1 |1

DCT4 | 1 | 1

WD2 | 1 | 1

BB5 | 1 OR 2 | 2

Posted in Uncategorized

አይሲዎችን መለየት ክፍል 2

ጥገና የሚጀምረዉ የተነገረን ችግር የመጣዉ ከየትኛዉ የስልካችን አቀማመጥ እንደሆነ ከመለየት ነዉ ። የተለያዩ ስልኮች የተለያየ አይሲ አቀማመጥ አላቸዉ ። ነገር ግን መሰረታዊ የሆነ መመሳሰል አላቸዉ ። የተለያዩ የሞባይል ብራንዶች የተለያየ አይሲ አወቃቀር ሲኖራቸዉ የTx1 Rx እና ፓወር ኤንድ ሎጂክ ክፍል አቀማመጥ ግን ተመሳሳይ አላቸዉ ። ከሌሎች ብራንዶች በተለየ ሁኔታ የኖኪያ ስልኮች በ4 በተለያዩ ትዉልዶች ከፍሎ ማየት ይቻላል ። እነኚህ ትዉልዶች DCT3 ,DCT4, WD2, እና BB5 ተብለዉ ይታወቃሉ ። ልዩነታቸዉ እንደሚከተለዉ ነዉ ።

Posted in Uncategorized

ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ክፍል 1

ስልካችን ከመጠገናችን በፊት የሃርድዌር እና የሶፍትዌር ሃሳብ ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ። ሀርድዌር ማለት ልናየዉ ልንዳስሰዉ የምንችለዉ የስልካችን የዉስጥም ሆነ የዉጪ ክፍል ማለት ነዉ ። ማንኛዉም የሀርድዌር ክፍል ትንሽም ሆነ ትልቅ የራሱ የሆነ ክብደትና ቀለም ይኖረዋል ። በሌላ አባባል የስልካችን የሃርድዌር ክፍል የሚዳሰስ ዕቃ ነዉ ማለት ነዉ ። ለምሳሌ ከቨር : የባትሪ ማስቀመጫ ክፍሉ : ስክሪን በተጨማሪ ስልካችን ተከፍቶ ወይም ከፈታነዉ በኋላ ልናያቸዉ የምንችል ማንኛዉም አይሲ: ሬዚስተር :ካፓሲተር :ኢንደክተር በሙሉ የስልካችን ሀርድዌር ክፍል ነዉ ።

ሶፍትዌር ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ማለት ነዉ ። ይህ ማለት በአይናችን የማናየዉ የማንዳስሰዉ ነገር ግን ስልካችን ስርአቱን ሳያዛባ እንዲሰራ የሚያደርግ መንገድ ማለት ነዉ ። የስልካችንን ሶፍትዌር እራሱን አንየዉ እንጅ ስራወቹን ማየት እንችላለን ለምሳሌ :- ስክሪናችን ላይ ስዓት : ምስል : የኔትወርክ ምልክት እንዲሁም ማንኛዉም ጥሁፍ እንዲመጣ እና እንዲሰራ የሚያደርገዉ ሶፍትዌሩ ነዉ ። እነኚህን ምስሎች ወይም ጽሑፎች በእጃችን መንካት አንችልም ። እነኚህን ጽሑፎችና ምስሎችን ለመንካት ብንሞክር ለመንካት የምንችለዉ የሀርድዌር ክፍል የሆነዉን ስክሪኑን ነዉ ።

አንድ ስልክ በስርአቱ እንዲሰራልን ሁለቱም ክፍሎች ማለትም ሀርድዌር እና ሶፍትዌር በአግባቡ መስራት አለባቸዉ ። አንዳቸዉ እንኳ ቢበላሹ ስልካችን በስርአቱ ሊሰራ አይችልም ። የሶፍትዌሩን ችግር ለመፍታት ፍላሸር ቦክስ ያስፈልገናል /ከኮምፒውተር በተጨማሪ/። አንዳንድ ጊዜ ቀለል ያሉ የሶፍትዌር ችግሮች በኮድ ልናስተካክላቸዉ እንችላለን ። ይህ ማለት የተወሰኑ ቁጥሮችን በማስገባት ችግሩን መፍታት እንችላለን ማለት ነዉ ። ምሳሌ :-ሪስቶር ማድረግ ።

የሀርድዌር ችግር ሲገጥመን እንደችግሩ አይነትና መጠን መፍቻ : ካዉያ : ዲሲ :ቲነር: ብሎወርና የመሳሰሉትን መሣሪያዎች በመጠቀም እንጠግናለን የአንዳንድ የማይበራ ወይም ጸጥ ያለ ስልክ ችግር ሶፍትዌር ነው ወይም ሃርድዌር ነዉ ብሎ ለመለየት ስልኩ የሚያሳየንን ምልክት በማየት ወይም ዲሲ ፓወር ሰፕላይ በመጠቀም ማወቅ ይቻላል ። የስልካችንን ሶፍትዌር ወደ ተሻለ ፕሮግራም መቀየር /upgrade/ ማድረግ እንችላለን ።

አንዳንድ ጊዜ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ሃሳብ በተሳሳተ መንገድ ሲገለጽ ይስተዋላል ።

ሃርድዌር ማለት የሚታይ ክፍል ሶፍትዌር ደግሞ የማይታይ ክፍል ብሎ ማስቀመጥ የተሳሳተ ነዉ ። ምክንቱም የስልኮችን የሶፍትዌር ስራ ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ :- የስልኮች ስክሪን ላይ የምናየዉ የኔትወርክ ምልክት : ቀን : ስአትና ሜኑ: ስክሪንሴቨር: ጋለሪ: ፎቶግራፎች የመሳሰሉትን የሶፍትዌር ስራዎች ማየት ይቻላል ።

ሆኖም የአንድን ስልክ ሶፍትዌር ፕሮግራሙን ማየት ግን አይችልም ። ስለዚህ የሚታይ ክፍል እና የማይታይ ክፍል ብሎ ከመለየት ይልቅ ሃርድዌር የሚዳሰስ እና ሶፍትዌር የማይዳሰስ ክፍል ብሎ መለየት የተሻለነዉ ።