Posted in Uncategorized

የተለያዩ ኔትወርክ የመላክና የመቀበል ሂደት ክፍል 10

የመላክ ሂደት

የመላክ ሂደት የሚጀመረዉ ከማይክ ነዉ ። የማይክ ስራ ድምጻችንን ወደ ወደ ኤሌክትሪክ ሞገድ መቀየር ነዉ ።ከማይክ የሚወጣዉ ድምጽ ወደ ኦድዩ አይሲ ይሄዳል ። ኦድዩ አይሲ ይህንን የኤሌክትሪክ ሞገድ ያጎዳዋል ። በሌላ አነጋገር ጉልበት ይሰጠዋል ። ከኦዲዩ አይሲ የሚወጣዉ የኤሌክትሪክ ሞገድ ቀጥታ ወደ አየር ቢልከዉ ከሌሎች ሞገዶች ጋር በመደባለቅ እዚያዉ አየር ላይ ይቀራል ። ስለዚህ ኔትወርክ አይሲ ቪሲኦን ተሸካሚ ሲግናል እንዳያመርትለት ያዘዋል ። ኔትወርክ አይሲም ተሸካሚ ሲግናል እና የድምጽ መልእክት እንዲደባለቁ ያደርጋል ። ይህ የማደባለቅ ሂደት ሞጁሌሽን ይባላል ። ይህን የተቀላቀለ ሞገድ (ኔትወርክ) ወደ ፓዎር አምፕሊፋየር ይልከዋል ።

የመቀበል ሂደት

የመቀበል ሂደት የሚጀመረው ከአንቴና ነዉ ። አንቴና የተቀበለዉን ኔትወርክ ወደ አንቴና ስዊች ይልካል ። ኔትወርክን በምንልክበት ጊዜ አንቴና ስዊች የተጨናነቀዉንና ነፃ የሆነዉን መስመር ይመርጥልናል። በመቀበል ሂደት ግን የማለፊያ መንገድ ነዉ ። ይህም ማለት የመምረጥን ስራ አይሰራም ማለት ነዉ ። ይህም የሚሆነው የሚደዉልልን ሰዉ ስልክ የተሻለዉን ወይም ነፃ የሆነዉን መስመር መርጦ ስለሚልክልን ነዉ ።

አንቴና ስዊች የተቀበለዉን የኔትወርክ ሞገድ ወደ ኔትዎርክ አይሲ ይልከዋል ። ኔትወርክ አይሲ ይህንን የተዋሃደ ሞገድ ወደ ተሸካሚ እና ኤሌክትሪክ ሞገድነት ይቀይረዋል ። በመላክ ሂደት ኔትወርክ አይሲ እነኝህን ሞገዶች ሲያጣምር ነበር ። በመቀበል ሂደት ደግሞ ይነጣጥላቸዋል ። የመነጣጠሉ ሂደት ዲሞጁሌሽን ይባላል ። ከዚህ የመነጣጠል ሂደት በኋላ ኔትወርክ አይሲ የኤሌክትሪክ ሞገዱን ወደ ኦዲዩ ይልከዋል ።