Posted in Uncategorized

የብርሀን /ላይት/ ጥገና ክፍል 17

የብርሃን ችግር በአራት ዋና ዋና ክፍሎች እንከፍለዋለን :- 1ኛ ችግር ምንም ብርሀን የሌለዉ ፤ 2ኛ ችግር ብርሃን ቀኑን ሙሉ የሚያበራ ወይም ምንም የማይጠፋ ፤ 3ኛ ችግር ስክሪን ላይ ብርሃን የሌለዉ ሲሆን ፤ 4ኛ ችግር ኪፓድ ላይ ብርሃን የሌለዉ ስልክ ነዉ ።

1.ምንም ብርሃን የሌለዉ

  • በዚህ ጊዜ መጀመሪያ የስልካችንን መቼት /ሴቲንግ/ እናያለን ። ባክላይት ኦፍ ከሆነ ወደ ኖርማል እንመልሰዋለን ። በመቀጠል ኪፓድ ኮኔክተርን እናያለን እግሮቹ ታጥፈዉ ወይም ተሰብረዉ ከሆነ ተገቢዉን ማስተካከያ እናደርጋለን ። ኮኔክተሮቹ ከቆሸሹ እናጸዳቸዋለን ። ችግሮቹን ለመፍታት እንዲመቸን ዲሲቲ 3 እና ሌሎቹን እናያለን ።
  • ዲሲቲ 3 ፦ የዲሲቲ 3 ስልኮች ብርሃን ቁጥጥር የሚደረገዉ በዩአይ አይሲ ነዉ ። ዩአይ አይሲ ሃያ እግሮች አሉት ። አንደኛዉ እግር ዩዩአይ አይሲ ላይ ከሚገኘዉ ትንሽ ነጥብ አጠገብ ይገኛል ። የዩአይ አይሲ 9ኛዉ እግር የእስክሪናችንን ብርሃን ይቆጣጠራል ። 13ኛዉ እግሩ ደግሞ የኪፓድ ብርሃንን ይቆጣጠራል ። የብርሃን ሰጪ ነ /LEDs/ ፖዘቲቭ እግር እና የዩአይ አይሲ አንደኛዉ እግር ከባትሪ ፖዘቲቭ ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት አላቸዉ ።
  • ከላይ የተጠቀሱት ግንኙነቶች በመልቲ ሜትር ፈልገን የተቋረጡ መንገዶች ካሉት በጃምፐር እናገኛቸዋለን ። ይህንን አድርገን ችግሩ የማይፈታ ከሆነ ችግሩ ያለዉ ዩአይ አይሲ ላይ ስለሆነ ለመቀየር እንገደዳለን ማለት ነዉ ።

2.መብራቱ በጭራሽ የማይጠፋ ስልክ

  • የዚህ ችግር ምክንያት የሚሆነዉ ላይት አይሲዉ ዉስጥ ሾርት ሰርኪዉት / ሁለት መገናኛ የሌለባቸዉ /መስመሮች ሲገናኙ ነዉ ። ስልኩ ዲሲቲ 3 ከሆነ ዩአይ አይሲ ይቀየራል ። ስልኩ ዲስቲ ፎር ፣ ደብሊዉ ዲቱ ወይም ቢቢ ፋይቭ ከሆነ ላይት አይሲዉን መቀየር ብቸኛዉ መፍትሄ ነዉ ።

3.ስክሪኑ ላይ ብርሃን የሌለዉ ነገር ግን ኪፓዱ ላይ ብርሃን ያለዉ ስልክ

የዚህ ስልክ ችግር ላይት ወይም ቡስተር ኮይል የሚሆንበት አጋጣሚ የለም ማለት ይቻላል ። ምክንያቱም ከሁለቱ አንዱ እንኳን መስራት ቢያቆም ሌላ ችግር ቢኖርበት ኪፓዱ ላይ ብርሃን ማየት አንችልም ነበር ። ስለዚህ ችግሩ የሚሆነዉ ከላይት አይሲ እና ከቡስተር ኮይል ወደ ስክሪን የሚወስደዉ መንገድ ላይ የተቋረጠ መስመር አለ ማለት ነዉ ። ለዚህ ችግር መፍትሔ ሊሆን የሚችለዉ :-

  1. ስክሪኑን በመቀየር መሞከር
  2. ስክሪን ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ
  3. የተጣመመ ወይም የተሰበረ እግር ካለዉ ማስተካከል
  4. ስክሪን ኮኔክተሩን መቀየር
  5. ከላይት አይሲ ካፓሲተር ወይም ከላይት እግር እስከ ስክሪን የተቋረጠ መስመር ካለ ተመሳሳይ ቦርድ በመጠቀም ወይም ሃርድ ላይብረሪ በመጠቀም መለየት እና በጃምፐር ማያያዝ የመጨረሻ መፍትሄ ይሆናል ።

ኬብል ያለዉ ስልክ ከሆነ ኬብል በመቀየር መሞከር ችግሩ ካልተፈታ ኬብል ኮኔክተሮቹን ማፅዳት ወይም መቀየር መፍትሔ ይሆናል ።

4.ኪፓዱ ላይ ብርሃን የሌለዉ ነገር ግን ስክሪኑ ላይ ብርሀን ያለዉ ስልክ

ከላይ ቁጥር 3 ላይ በተገለፀዉ መንገድ የዚህ ችግር መንስኤ ሊሆን የሚችለዉ የኪፓድ ላይቶች መላሸት ወይም የኪፓድ ኮኔክተር ችግር ነዉ ።

  1. ኪፓድ ላይቶችን በመልቲ ሜትር ማየት /መልቲሜትር ኮንቲኒቲ ከጫፍና ጫፍ ስናደርግባቸዉ መብራት ይሰጣሉ /
  2. ኪፓድ ኮኔክተሩን በቲነር ማጠብ
  3. ኪፓድ ኮኔክተሩ የተጣመመ ወይም የተሰበረ እግር ካለዉ ማስተካከል
  4. ኪፓድ ኮኔክተሩን መቀየር