Posted in Uncategorized

LNB ምንድን ነዉ?

አንብበዉ ሲጨርሱ ላይክ እና ሼር ማድረግዎን አይርሱ ።

LNB በእንግሊዘኛ አህፅሮተ ቃል ሲሆን ሲተነተን (Low Noise Black) የሚለዉን የእንግሊዘኛ ቃል ይይዛል ። LNB የራዲዩ ሞገድን ከዲሽ ላይ በመቀበል ወደ ሲግናል ከቀየረ በኋላ በኬብል አማካኝነት ወደ ሪሲቨሮች የሚልክ የዲሽ አናተ ላይ የሚገጠም መሳሪያ ነዉ ።

የLNB አይነቶች ስንት ናቸዉ?

በመሰረታዊነት አገራችን ዉስጥ የሚስተዋሉ የLNB አይነቶች ሁለት ቢሆኑም የዘርፍ ባለሙያዎች ግን በአለም ላይ 4እና ከዚያ በላይ እንደሆኑ ያስረዳሉ ። ለመሆኑ አገራችን ዉስጥ በስፋት ጥቅም ላይ የሚዉሉ የLNB አይነቶች እነማን ናቸዉ እስኪ እንመልከታቸው ። ብዙ ሰዎችም በእነዚህ በሁለቱ መካከል ያለዉ ልዩነት ሲያወዛግባቸዉ እንመለከታለን።

ሀ.KU Band LNB

በተለምዶ ku band የሆኑ ፍሪኩየንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነዉ ።

12522

ባህሪያቸዉ

  • ባለ 5 ዲጅት ፍሪኩየንሲን ይቀበላል ።
  • የፍሪኩዌንሲዉ ሳት ከ11200 – 12220 GHz ነዉ ።
  • ትልቅ የፍሪኪዌንሲ መጠን መያዛቸዉ አጭር የሞገድ ርዝመት እንዲኖራቸዉ አድርጓቸዋል ።
  • በአጭር ሞገድ ርዝመት መስራታቸዉ በትንንሽ ዲሾች (offeset dishes) እንዲሰሩ አስችሏቸዋል ። ለምሳሌ ፦ (ዲያሜትራቸዉ ከ30-65 ሳ.ሜ የሆኑ ዲሾች ላይ እንዲሰሩ አአስችሏቸዋል ።)
  • በዚህም የተነሳ ብዙ አገራችን የማይሸኑ ከመሆናቸዉም በላይ ለተለዋዋጭ ጸባይ ተጋላጭ ናቸዉ ። (ለምሳሌ እንደ ዝናብ እርጥበት አዘል አየር ……. ወ.ዘ.ተ)
  • በLNBወ ዉስጥ የሚኖረዉ እርግብግቦሽ መጠን ከፍ ሲል 10600 እንዲሁም ዝቅ ሲል 9750 ነዉ ። አለማቀፋዊ የሆኑ KU Band LNBዎች የLNB frequency 9750 10600 ነዉ ።

ለ. C Band LNB

  • በተለምዶ C Band የሆኑ ፍሪኮንሲዎችን ለመቀበል የሚያስችል መሳሪያ ነዉ ።

4103

ባህሪያቸዉ

  • ባለ 4 ዲጅት ፍሪኪዌንሲ ይቀበላል ።
  • የፍሪኪዌንሲ ወሰኑ ከ3700 – 4200 GHz ነዉ።
  • ትንሽ የፍሪኪዌንሲ መጠን መያዛቸዉ ረጅም የሞገድ ርዝመት እንዲኖራቸዉ አድርጓል ።
  • በረጅም ሞገድ ርዝመት መስራታዉቸዉ የግዴታ ትልልቅ መጠን ላላቸዉ ዲሾችን (prime focus dishes) እንዲጠቀሙ አድርጓቸዋል ።
  • ይህም የሳተላይት ሽፋኑ ብዙ አገራችን እንዲያካልል ከማገልገሉም በላይ ተለዋዋጭ የአየር ፀባይ እንዳይጋለጡ አግዟቸዋል ።
  • ብዙ አገራችን እንደማካለላቸዉ መጠን አብዛኛወቹ ቻናሎች አለማቀፋዊ ቋንቋን ይጠቀማሉ ይዘታቸውም በዚያዉ ልክ መልካም የሚባል ነዉ ።
  • በLNBወ ውስጥ የሚኖረዉ የርግብግቦሽ መጠን ጫፍ ሲሆን 5150 ነዉ ።

ለተጨማሪ መረጃ

0945-68-63-10

ኑሩ ዲሽ የዲሽ እዉቀትዎን ያሳድጉ