Posted in Uncategorized

ሃርድዌር እና ሶፍትዌር ክፍል 1

ስልካችን ከመጠገናችን በፊት የሃርድዌር እና የሶፍትዌር ሃሳብ ምን እንደሆነ ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ። ሀርድዌር ማለት ልናየዉ ልንዳስሰዉ የምንችለዉ የስልካችን የዉስጥም ሆነ የዉጪ ክፍል ማለት ነዉ ። ማንኛዉም የሀርድዌር ክፍል ትንሽም ሆነ ትልቅ የራሱ የሆነ ክብደትና ቀለም ይኖረዋል ። በሌላ አባባል የስልካችን የሃርድዌር ክፍል የሚዳሰስ ዕቃ ነዉ ማለት ነዉ ። ለምሳሌ ከቨር : የባትሪ ማስቀመጫ ክፍሉ : ስክሪን በተጨማሪ ስልካችን ተከፍቶ ወይም ከፈታነዉ በኋላ ልናያቸዉ የምንችል ማንኛዉም አይሲ: ሬዚስተር :ካፓሲተር :ኢንደክተር በሙሉ የስልካችን ሀርድዌር ክፍል ነዉ ።

ሶፍትዌር ማለት ስልካችን የሚሰራበት ፕሮግራም ማለት ነዉ ። ይህ ማለት በአይናችን የማናየዉ የማንዳስሰዉ ነገር ግን ስልካችን ስርአቱን ሳያዛባ እንዲሰራ የሚያደርግ መንገድ ማለት ነዉ ። የስልካችንን ሶፍትዌር እራሱን አንየዉ እንጅ ስራወቹን ማየት እንችላለን ለምሳሌ :- ስክሪናችን ላይ ስዓት : ምስል : የኔትወርክ ምልክት እንዲሁም ማንኛዉም ጥሁፍ እንዲመጣ እና እንዲሰራ የሚያደርገዉ ሶፍትዌሩ ነዉ ። እነኚህን ምስሎች ወይም ጽሑፎች በእጃችን መንካት አንችልም ። እነኚህን ጽሑፎችና ምስሎችን ለመንካት ብንሞክር ለመንካት የምንችለዉ የሀርድዌር ክፍል የሆነዉን ስክሪኑን ነዉ ።

አንድ ስልክ በስርአቱ እንዲሰራልን ሁለቱም ክፍሎች ማለትም ሀርድዌር እና ሶፍትዌር በአግባቡ መስራት አለባቸዉ ። አንዳቸዉ እንኳ ቢበላሹ ስልካችን በስርአቱ ሊሰራ አይችልም ። የሶፍትዌሩን ችግር ለመፍታት ፍላሸር ቦክስ ያስፈልገናል /ከኮምፒውተር በተጨማሪ/። አንዳንድ ጊዜ ቀለል ያሉ የሶፍትዌር ችግሮች በኮድ ልናስተካክላቸዉ እንችላለን ። ይህ ማለት የተወሰኑ ቁጥሮችን በማስገባት ችግሩን መፍታት እንችላለን ማለት ነዉ ። ምሳሌ :-ሪስቶር ማድረግ ።

የሀርድዌር ችግር ሲገጥመን እንደችግሩ አይነትና መጠን መፍቻ : ካዉያ : ዲሲ :ቲነር: ብሎወርና የመሳሰሉትን መሣሪያዎች በመጠቀም እንጠግናለን የአንዳንድ የማይበራ ወይም ጸጥ ያለ ስልክ ችግር ሶፍትዌር ነው ወይም ሃርድዌር ነዉ ብሎ ለመለየት ስልኩ የሚያሳየንን ምልክት በማየት ወይም ዲሲ ፓወር ሰፕላይ በመጠቀም ማወቅ ይቻላል ። የስልካችንን ሶፍትዌር ወደ ተሻለ ፕሮግራም መቀየር /upgrade/ ማድረግ እንችላለን ።

አንዳንድ ጊዜ የሀርድዌርና ሶፍትዌር ሃሳብ በተሳሳተ መንገድ ሲገለጽ ይስተዋላል ።

ሃርድዌር ማለት የሚታይ ክፍል ሶፍትዌር ደግሞ የማይታይ ክፍል ብሎ ማስቀመጥ የተሳሳተ ነዉ ። ምክንቱም የስልኮችን የሶፍትዌር ስራ ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ :- የስልኮች ስክሪን ላይ የምናየዉ የኔትወርክ ምልክት : ቀን : ስአትና ሜኑ: ስክሪንሴቨር: ጋለሪ: ፎቶግራፎች የመሳሰሉትን የሶፍትዌር ስራዎች ማየት ይቻላል ።

ሆኖም የአንድን ስልክ ሶፍትዌር ፕሮግራሙን ማየት ግን አይችልም ። ስለዚህ የሚታይ ክፍል እና የማይታይ ክፍል ብሎ ከመለየት ይልቅ ሃርድዌር የሚዳሰስ እና ሶፍትዌር የማይዳሰስ ክፍል ብሎ መለየት የተሻለነዉ ።

ደራሲ ፥

ሙሉ የዲሽ እና የሞባይል ጥገና መረጃዎች ከኑሩ ዲሽ

አስተያየት ያስቀምጡ