Posted in Uncategorized

ተጨማሪ እዉነታዎች ክፍል 5

  1. ኖኪያ SL3 ስልኮች ላይ CPU ከሚሞሪ አይሲ ጋር አንድ ላይ ከተገኘ ወርቃማ እግር ላይኖረዉ ይችላል ።
  2. የቻይና ስልኮች ቻርጅ አይሲ አጠገብ የሚገኘዉ ሬዚስተር የተጻፈበት ቁጥር 22 የማይሆንበት ጊዜ አለ ። 220,470,477 ወይም ሌላ ቁጥር ሊሆን ይችላል ።
  3. ሳምሰንግ : ኤልጂ እና ሞቶሮላ ስልኮች ላይ R22 ላይገኝ ይችላል ። በዚህ ጊዜ ቻርጅ አይሲ አነስ ብሎ የሚገኝ እና አንድ እግሩ ከባትሪ ኮንቲኒቲ የሚሠጠዉ አይሲ ነዉ ።
  4. BB5 ስልኮች ቻርጅ አይሲ ኦግዚለር ፓወር አይሲ ስለሆነ R22 የለዉም ።
  5. ቪሲኦ ከኔትወርክ አይሲ ጋር አንድ ላይ ሊገኝ ይችላል ።
  6. SL3 ስልኮች ላይ ክሪስታል ኦሲሌተር ከCPU ጋር አብሮ ሊኖር ይችላል ።
  7. ኔትወርክ አይሲ ከቪሲኦ እና ከክሪስታል ኦሌሲተር በተለየ ጥቁር ቀለም ሲኖረዉ በመጠን ከሁለቱም አይሲዎች ይበልጣል ።
  8. የኤፍ ኤም አይሲ 1: 2 ወይም 3 ባለ ቀለም ኢንደክተር ሊከበዉ ይችላል ።
  9. አንዳንድ ስልኮች ላይ ብሉቱዝ አይሲ ከሬዲዮ አይሲ ጋር አንድ ላይ ይገኛል ።
  10. የቻይና ስልኮች በሙሉ እና የተወሰኑ ሳምሰንግ ስልኮች አርቲሲ ከኤምፒዩ አጠገብ ይገኛል ። የሌሎች ስልኮች RTC ግን ከፓወር አይሲ አጠገብ ይገኛል ።
  11. ካፓስተሮች በአብዛኛዉ ቡኒ ቀለም ሲኖራቸዉ ፊልተር ካፓሲተሮች ቢጫ በብርቱካናማ ወይም ጥቁር በግራጫ ቀለም ይኖራቸዋል ።
  • ደራሲ ፥

    ሙሉ የዲሽ እና የሞባይል ጥገና መረጃዎች ከኑሩ ዲሽ

    አስተያየት ያስቀምጡ