Posted in Uncategorized

አይሲዎች እና ግልጋሎታቸዉ ክፍል 6

  1. ሲፒዉ:- የስልኩን ሁለተናዊ እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል ። ይህን ስንል ስልካችን ዉስጥ የሚደረጉ ስራዎችን በሙሉ ለምሳሌ ቻርጅ ማድረግ : መደወል : መቀበል : አላርም : ካልኩሌተር : ካሌንደር የመሳሰሉት ይቆጠራል።
  2. ፓወር አይሲ :- ለእያንዳንዱ የስልክ አካል የሚገባዉን ያህል ከባትሪ ወስዶ ያከፋፍላል ። ለምሳሌ :- ለአንቴና ስዊች : ለሲፒዩ : ለክሪስታል ኦሲሌተር : ለኔትወርክ አይሲ እና ለሌሎች ክፍሎች በሙሉ የሚፈልጋቸዉን ሀይል ይሰጣል ።
  3. ኦዲዮ አይሲ :- የኤሌክትሪክ ሲግናልን (ሞገድን) የማጉላት ስራ ይሰራል ። የኤሌክትሪክ ሲግናሉ የድምጽ መረጃ የያዘ ነዉ ። ኦዲዮ አይሲ ስልካችን ዉስጥ የሚከናወኑ የድምጽ ሂደቶች በሙሉ ያጎላል ። ለምሳሌ :- እኛ የምናወራዉን ድምፅ እና የመሳሰሉትን በሙሉ በበቂ ሁኔታ እንዲሰሙ ያደርጋል ።
  4. ቻርጅ አይሲ :- ስልካችን ቻርጅ የሚደረግበት ጊዜ ከቻርጀር የሚመጣዉን ቮልቴጅ ወይም ሃይል መጥኖ ለባትሪ የማድረስ ስራ ይሰራል ። ቻርጅ አይሲ በቻርጅ እና ባትሪ መሀል ሆኖ ቮልቴጅ በተመጣጣኝ ሁኔታ ከቻርጀር ወደ ባትሪ እንዲሄድ ያደርጋል ። ቻርጀር—>ቻርጀር አይሲ—–>ባትሪ
  5. ሚሞሪ አይሲ :- ሚሞሪ አይሲ የተለያዩ መረጃዎችን የሚይዝ አይሲ ነዉ ። ሚሞሪ አይሲ በሁለት ይከፈላል ። ሁለት ክፍሎች ራምና ሮም በመባል ይታወቃል ። 5.1 ራም:- ራም የሚለዉ የሚሞሪ ክፍል ጊዜያዊ /ቋሚ ያልሆኑ / መረጃዎችን ያስቀምጣል ። ለምሳሌ ሚስኮል የተደረገን ቁጥር ፣ የደወልንበት ቁጥር እና ጥሪ የተቀበልንበት ቁጥር የሚቀመጥበት ክፍል ነዉ ። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎችን የምናገኛቸው እስከ ተወሰነ ቁጥር ብቻ ነዉ ። ከአንድ ወር ወይም ከሁለት ወር በፊት የደወልንባቸዉን ቁጥሮች አናገኛቸዉም ምክንያቱም የስልኩ ራም መያዝ እስከሚችለዉ ይይዝና ቀሪዉን በራሱ ያጠፋዋል ። ይህን መረጃ የመያዝ አቅም ደግሞ እንደ ስልኩ ሞዴል ይለያያል ። 5.2 ሮም:- ሮም የሚባለዉ ደግሞ ቋሚ የሆኑ እና እስካላጠፋናቸዉ ድረስ በፍጡም የማይጠፋ መረጃዎችን ይይዛል ። ለምሳሌ ፎቶ ግራፍ ፣ ሙዚቃ ፣ ቪድዮ ፣ የስልክ ቁጥሮችና የስልካችን ሶፍትዌር የሚቀመጡት ሮም ዉስጥ ነዉ ። ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች እስከፈለግነዉ ጊዜ ድረስ ማቆየት እንችላለን ። በአንድ ወቅት የተነሳነዉን ፎቶ ካላጠፋነዉ እስከፈለግነዉ ጊዜ ሳይሰረዝ ማቆየት እንችላለን ። ምክንያቱም ፎቶ ግራፍ የሚቀመጠው ሮም ዉስጥ ነዉ ።
  6. ዩአይ አይሲ :-

1. ሪንገርን

2. ቫይብሬተርን

3. የስክሪን ብርሃንን እና

4. የኪፓድ ብርሃንን ይቆጣጠራል ።

7. ረዳት ፓወር አይሲ :- ቢቢ ቫይቭ (BB 5) ስልኮች ዉስጥ ሁለት ፓወር አይሲ እንደሚገኝ ከላይ ተጠቅሷል ። ከአር ቲ ሲ አጠገብ የሚገኘዉ ዋና ፓወር አይሲ ሲሆን ከቡስተር ኮይል አጠገብ የሚገኘዉ ረዳት ፓወር አይሲ ነዉ ። ይህ አይሲ የቻርጅን እንቅስቃሴ እና የቮልቴጅን ሂደት ይቆጣጠራል ።

ደራሲ ፥

ሙሉ የዲሽ እና የሞባይል ጥገና መረጃዎች ከኑሩ ዲሽ

አስተያየት ያስቀምጡ